አባቶች በጋራ የሚኖሩበት፣ በጋራ የሚጸልዩበት፣ በጋራ የሚሠሩበት የአንድነት ገዳም
በማእከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፣ በምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ቤተክህነት፣ ከጎርጎራ ከተማ 5 ኪሎሜትር …. በቅዱሳን ገዳማት እንደ ከዋክብት በታጠረው በታላቁ ጣና ሐይቅ ዳርቻ… በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንዱና ቀዳሚው መንፈሳዊ ማዕከል ይገኛል። በ1326 ዓ/ም የተመሠረተዉ ማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም፡፡ ይህ የወንዶች ገዳም በቀድሞ የቦታው ስም “መድበይ”፤ በኋላም “ደብር ቅዱስ” ተብሎ ይጠራ ነበር።
ገዳሙ ይህንን ታላቅ የበረከት ሥጦታ በማቅረብ፣ ምዕመናን በጉልበታቸው፣ በገንዘባቸው እና በእውቀታቸው አስተዋጽዖ በማድረግ የታሪክና የበረከት ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪ እያቀረበ ነው።
የእመ ቅዱሳንን ቤተ ክርስቲያን የመገንባት ታላቅ መንፈሳዊ ሥራ የእርስዎንም አስተዋፅዖ በአክብሮት ይጠብቃል! በዚህ የተቀደሰ ፕሮጀክት ላይ የበኩልዎን በማበርከት ከእመቤታችን እና ከጻድቁ አቡነ ያሳይ ዘንድ የቃል ኪዳኑ ተሳታፊ ይሁኑ።
በመላው አለም የምትገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች፤ የታሪካዊቷ ቅድስት ኩክ የለሽ ማርያም ገዳም ወዳጆችና ቤተሰቦች፣ በቅድሚያ በፈጣሪ ሥም የከበረ ሠላምታዬን አቀርባለሁ።
በረከትዋ በአለም የተነገረላት በምልጅዋና በፈዋሽነቷ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን የመሠከሩላት እመቤታችን ኩክ የለሽ ማርያም ገዳም የተደቀነባትን የመሰንጠቅና የመሬት መደርመስ አደጋ በልጆቿ ትብብር ይቀለበስ ዘንድ ሁላችንም ርብርብ እንድናረግ በታላቅ ክብርና አደራ እጠይቃለሁ።
ሠላም ፍቅርና መተሳሰብ ለሀገራችን ይሁን።